Infographics

በበርካታ ሀገራት በፍጥነት የተስፋፋው የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ በየሀገራቱ ሊካሄዱ ቀን ተቆርጦላቸው ለነበሩ ሁነቶች መስተጓጎል ምክንያት ሆኗል። ዓለም አቀፉ የዲሞክራሲ እና የምርጫ ድጋፍ ኢንስቲትዩት (IDEA) ባለፈው ሳምንት ባወጣው መረጃ መሰረት ወረርሽኙ በ21 ሀገራት ሊካሄዱ የነበሩ ምርጫ ነክ ሁነቶች ላይ ጉልህ ተጽዕኖ በማሳደሩ ለሌላ ጊዜ እንዲተላለፉ አስገድዷል። 

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድም የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ “በመራጮች ትምህርት፣ የምርጫ አስፈጻሚዎች ስልጠና እና የቁሳቁስ ስርጭትን” ላይ ተጽዕኖ ሊያሳድር እንደሚችል ባለፈው ሳምንት መጨረሻ አስታውቋል። በእነዚህ ተግባራት ላይ የሚደርስ መስተጓጎል በምርጫ የጊዜ ሰሌዳው ላይ ቀጥተኛ ተጽእኖ ኧእንደሚኖረው መገለጹ ይታወሳል። ከታች የሚመለከቱት ምስላዊ መረጃ በኮሮና ቫይረስ ሳቢያ የምርጫ ሁነቶቻቸውን ያራዘሙ የ10 ሀገራትን ሁኔታ ያሳያል። (ኢትዮኢሌክሽን)


የብልጽግና ፓርቲ የምርጫ የጸጥታ ሁኔታ ግምገማ 


ገዢው የብልጽግና ፓርቲ፤ ምርጫውን የተመለከቱ አቅጣጫዎች የሰፈሩበትን ሰነድ፤ ለመካከለኛ አመራሮቹ ባለፈው የካቲት ወር አጋማሽ አሰራጭቶ ነበር። ፓርቲው “ሀገራዊ የለውጥ እርምጃዎች” በሚል ርዕስ ለ40 ሺህ ገደማ ለሚሆኑ ለመካከለኛ አመራሮቹ ስልጠና ባዘጋጀው ሰነድ ላይ በኢትዮጵያ መጥቷል የሚለውን ለውጥ “ምንነት እና ስኬቶቹን” ተንትኗል። በሀገር ደረጃ ያጋጥማሉ ያላቸውን “ቀጣይ ፈተናዎች እና መሻገሪያ ስልቶችን” አመላክቷል። በዚህ ሰነድ ማገባደጃ ላይ የ2012ቱ ሃገራዊ ምርጫ ጉዳይም በ11 ገጾች ተዳስሷል። ከምርጫ ዝግጅት እስከ ድህረ ምርጫ ያሉ ሂደቶችን የተመለከተው የፓርቲው ሰነድ በምርጫ ወቅት ሊያጋጥሙ ይችላሉ ያላቸውን ተግዳሮቶች በዝርዝር አስቀምጧል። (ኢትዮኢሌክሽን)


ስለ ምርጫ ምን ተባለ?


ቁጥሮች፦ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የምርጫ በጀቱን ሲያዘጋጅ የመራጮች ቁጥር 53.9 ሚሊዮን ይደርሳል በሚል ግምት ነበር። እንደ ቦርዱ ግምት በቀጣዩ ምርጫ 45.3 ሚሊዮን ህዝብ ለመራጭነት ይመዘገባል ተብሎ ይጠበቃል።

ስለ ምርጫ ምን ተባለ?

በኢትዮጵያ በአምባሳደርነት ያገለገሉ 4 የአሜሪካ ዲፕሎማቶች በሰኔ 2011 በኢትዮጵያ ወቅታዊ ጉዳይ ላይ ባደረጉት ውይይት በሀገሪቱ በሚቀጥለው ዓመት ይካሄዳል ተብሎ ስለሚጠበቀው ምርጫ ተጠይቀው የየራሳቸውን አስተያየት አካፍለዋል። በአሜሪካ የሰላም ኢንስቲትዮት አዘጋጅነት በዋሽንግተን ዲሲ በተካሄደው ውይይት ጠንከር ያለ ሀሳብ ያነሱት ዴቪድ ሺን ናቸው።
ሺን ኢትዮጵያ “ምርጫ ለማካሄድ ዝግጁ አይደለችም” የሚል ዕምነት ያላቸው ይመስላል። ዶናልድ ቡዝ ኢህአዴግ ከምርጫ 97 ወዲህ ባልተጠበቀ ውጤት ዳግም መደንገጥ እንደማይፈልግ አስታውሰው ከጠቅላይ ሚኒስትር አብይ መምጣት ወዲህ ግን ነገሮች የተቀየሩ እንደሚመስሉ አትተዋል።
በምርጫ 97 ወቅት በኢትዮጵያ የአሜሪካ አምባሳደር የነበሩት ኦሪሊያ ብራዚል ቀጣዩን ምርጫ እርሳቸው ከታዘቡት ጋር ማነጻጸርን መርጠዋል። በመረጃ ማግኘት በኩል ሰፊ ልዩነት እንዳለም ገልፀዋል። በሽግግሩ ወቅት አዲስ አበባ የነበሩት ማርክ ባስ የምርጫ ሂደቱ ላይ ትኩረት መስጠት እንደሚገባ አሳስበዋል። ሂደቱንም ኢትዮጵያውያን ራሳቸው በባለቤትነት መምራት ይገባቸዋል የሚል ዕምነታቸውን አንፀባርቀዋል።


ሐምሌ 1, 2011 በጸደቀው የ2012 የፌደራል መንግስት በጀት፤ ለምርጫ ኦፕሬሽን እና ሎጀስቲክ ስራዎች ማከናወኛ፤ 2.25 ቢሊየን ብር ተመድቧል። ገንዘቡ ለብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ጽህፈት ቤት በተለቀቀው በጀት ውስጥ የተካተተ ነው።

የካበተ የዳኝነት ልምድ ያላቸው አቶ ውብሸት አየለ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የስራ አመራር ቦርድን በምክትል ሰብሳቢነት እንዲመሩ ተሹመዋል። ከአምስቱ የኢትዮጵያ ምርጫ ቦርድ የስራ አመራር አባላት ሁለቱ ሴቶች ናቸው ፦ ብዙወርቅ ከተተ እና ሰብሳቢዋ ብርቱካን ሚደቅሳ። ዶ/ር አበራ ደገፋ በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ከ20 ዓመታት በላይ ሲያስተምሩ የቆዩ ሲሆን በተመሳሳይ ዶ/ር ጌታሁንም በዩኒቨርስቲ የህግ መምህር ነበሩ። ዶ/ር ጌታሁን በማማከር ስራም ሰፊ ልምድ አላቸው።


የተወካዮች ምክር ቤት ሰኔ 6, 2011 ባካሄደው መደበኛ ስብሰባው ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ለምርጫ ቦርድ የስራ አመራር ቦርድ የመረጧቸውን 4 አዳዲስ አባላትን ሹመት አፅድቋል። ተሿሚዎቹ ብዙወርቅ ከተተ፣ ውብሸት አየለ፣ ዶ/ር አበራ ደገፋ እና ዶ/ር ጌታሁን ካሳ ናቸው። ከእነዚህ አዳዲስ የስራ አመራር ቦርድ አባላት በተጨማሪ የምርጫ ቦርድ ሰብሳቢዋ ብርቱካን ሚደቅሳም በኃላፊነታቸው እንዲቀጥሉ የተወካዮች ምክር ቤት ወስኗል። የሰኔ ስድስቱን ሹመት እና ውሳኔ 17 የፓርላማ አባላት ተቃውመውታል።

ብሔራዊ ምርጫ – 547 የፓርላማ መቀመጫዎች – ዘጠኝ ክልሎች እና ሁለት የከተማ አስተዳደሮች – ምርጫ 2012